EthiopiaNews

የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምረቃ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን አዲሱን የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ በይፋ መርቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ  እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው  መሆኑን ገልፀው  በሳምንት ሦስት በረራዎችን እንደሚያስተናግድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር እንደሚፈጥር እና  የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው።

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv