የንግድ ሥነ-ሥርዓት እርምጃው ቀጥሏል
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ መንግስት እየወሰደኩት ነው ባለው የሥነ-ሥርዓት እርምጃ የ36 ንግድ ተቋማት ንግድ ፍቃድ ተሰርዟል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተዋል ባላቸው 7676 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ያስታወቀ ሲሆን የ42 ንግድ ተቋማት ፈቃድ ማገዱን እና በ286 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ የእስራት ቅጣት መጣሉን ገልጿል።