EthiopiaNews

የንግድ ባንክ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንኩ ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ከሚደውሉ አጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

የባንኩ ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል የሚደርሳቸውን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱ ባንኩ አስጠንቅቋል።

ባንኩ ደንበኞቹ የባንክ መረጃቸውን በስልክ ለማንም እንዳይሰጡ እና የባንኩን መተግበሪያዎች ከ ፕሌይ ስቶር እና አፕ ስቶር ብቻ አውርደው እንዲጠቀሙ መክሯል።

የባንኩ ደንበኞች ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ እንዲፈትሹ ባንኩ አሳስቧል።

መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv