EthiopiaNews

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር መገኘቱን አስታውቋል።

ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ( ዶ/ር ) ይሄን ያሉት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ላይ ነው።

ሚኒስትሩ ዘንድሮ ከወጪ ንግድ ዘርፍ የተገኘው ገቢ የዕቅዱን 114 በመቶ ማሳካት የቻለ ነው ብለዋል።

ሚነስትሩ በበጀት አመቱ ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦንላይን ተሰጥቷል ብለዋል።

አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ 804 አዳዲስ የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን በመጨመር በአጠቃላይ ቁጥራቸውን 2,369 ማድረስ ተችሏል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews