InternationalNews

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ

በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቱ እጩ የሆኑት ካምላ ሀሪስ የምርጫ አጋራቸውን ይፋ ሊያደርጉ ነው፡፡

በቀደመው ምርጫ የጆ ባይደን የምርጫ አጋር የነበሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሀሪስ ዛሬ በሚያካሂዱት የቅስቀሳ ዘመቻ የምርጫ አጋራቸውን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሀሪስ በምርጫው ካሸነፉ የምርጫ አጋራቸው ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ሲጠበቅ ለምርጫ አጋርነት ከታጩ በርካታ ዲሞክራቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከእጩዎች ውስጥም የአሪዞና ገዢ ቲም ዋልዝ፣ የአሪዞና ሴናተር ማርክ ኬሊ እና የፔንሰልቫኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጆሽ ሻፒሮ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ሀሪስ ይህን ይፋ ካደረጉ በኋላ ለቀጣይ አምስት ቀናት በቁልፍ የምርጫ ግዛቶች ቅስቀሳ እንደሚያካሂዱ ነው በቢቢሲ ዘገባ የተመለከተው፡፡