የአየር መንገዱ ሽልማት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፔክስ የመንገደኞች ምርጫ አዋርድ 2026 ‘የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ’ በመባል ተሸላሚ መሆኑን አስታወቀ።
ይህ ሽልማት አየር መንገዱ የተሳለጠ፣ ምቹ እና አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ያለውን ያልተቋረጠ ትጋት ከማሳየቱ ባሻገር በአቪዬሽን አገልግሎት ዘርፉ ያለውን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ መሸለሙ አስደሳች መሆኑን ገልፀው ሽልማቱ ይበልጥ እንዲተጋ በእጅጉ ያበረታተዋል ብለዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
