InternationalLatestNews

የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ6 የአፍሪካ አገራት

የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ6 የአፍሪካ አገራት በታዳሽ የሀይል ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች የ164 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ ።ይህ የ 164 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በኢትዮጵያ፣ ጋና ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ቱኒዚያ እና ጊኒ አገራት በታዳሽ የሀይል ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን ለማጠናከር የሚውል ነው ሲል ባንኩ በመግለጫ አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ልማት ባንክ የፀደቀው ይሄው ድጋፍ በ6 የአፍሪካ አገራት 6 ሚሊዮን ዜጐችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን እስከ 28 ሚሊዮን ቶን የሚመዝን የበካይ ጋዝ ልቀት እንዲቀንስ የሚረዳ መሆኑን አዲስ ነገር ከባንኩ ድረ ገፅ አይቷል።የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአለም አቀፉ “የግሪን ክላይሜት ፈንድ” ጋር በመተባበር እውን ያደረገው ድጋፉ በ 6ቱ የአፍሪካ አገራት የታዳሽ የሀይል ዘርፍ ይበልጥ እንዲስፋፋ ያደርጋል ሲሉ የባንኩ ሀላፊዎች ገልፀዋል::

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision