የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ( ኢሶዴፓ) በምርጫው ስሳተፍ በርከት ያሉ መሰናክሎች ገጥመውኝ ነበር ብሏል::

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ( ኢሶዴፓ) በምርጫው ስሳተፍ በርከት ያሉ መሰናክሎች ገጥመውኝ ነበር ብሏል:: ፓርቲው ገጥመውኝ ነበር ያላቸውን መሰናክሎች አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ በተለይ በምርጫው እለት ገዥው ፓርቲን በማስገደድ ምረጡ ተብሎ ነበር ሲል የከሰሰ ሲሆን የምርጫ ሳጥኖች ተሰብረው መገኘት ብሎም በፓርቲው እጩዎችና ታዛቢዎች ላይ የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት ደርሷልም ብሏል፡፡ በተጨማሪም በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ድምጽ አሰጣጡ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት መገፋቱን ሰበብ በማድረግ በተለይ በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የቀበሌና የወረዳ አመራሮች ድምፅ እንዲያጭበረብሩ አመች ሁኔታ ፈጥሮላቸው ነበር ሲል ገልጿል::ትከረቱን በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በ87 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ አድርጎ እንደተወዳደረ ያስታወሰው ኢሶዴፓ ገጠሙኝ ላላቸው መሰናክሎች ዋነኛ ምንጮች በቀበሌና በወረዳ የሚገኙ የበታች የመንግስት ሹማምንት ናቸው ሲልም ተደምጧል::