LatestNews

ፍርድ ቤት በጀነራል ሰአረ መኮንንና ብ/ጄ ገዛኢ አበራ ላይ ግድያ ፈጽሟል ባለው ተከሳሽ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት በየነ።

በዛሬው እለት የተሰየመው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጀነራል ሰአረ መኮንንና ብ/ጄ ገዛኢ አበራ ላይ ግድያ ፈጽሟል ባለው ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ላይ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት በየነ። የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን ተከሳሹ ባለፈው ግንቦት ወር 2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ከ ብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ጋር በመገናኘት ተልኮ ተቀብሎ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው፡፡ አስራለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፥ በሰኔ 15 በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት እነ ዶክተር አንባቸው መኮንን ላይ የተፈፀመ ግድያን ተከትሎ በስልክ በቤታቸው አመራርነት ሲሰጡ የነበሩት ጠቅላይ ኢታማዡር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኮንን እና ጓደኛቸው ብ/ጄ ገዛኢ አበራን በሽጉጥ ገሏል ተብሎ መከሰሱ ይታወቃል፡፡ ዓቃቢህግ ባቀረበው የ3 ገፅ ቅጣት ማክበጃ ተከሳሹ በሞት ይቀጣልኝ ሲል የጠየቀ ቢሆንም ችሎቱ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረበውን 4 የቅጣት ማቅለያ ማለትም የቤተሰብ አስተዳደሪ መሆኑን፣ በጤናው የደረሰ ጉዳትን፣ በልጅነቱ ውትድርና ተቀጥሮ ሀገርና ህዝብን ማገልገሉ፣ በቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕድሜልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ኢዚአ ዘግቧል፡፡