LatestNews

የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሀውልት በአንድ ሳምንት ውስጥ ይመረቃል

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ሰዓረ_መኮንን እና የአርቲስት #ሀጫሉ_ሁንዴሳ መታሰቢያ ሀውልት በአንድ ሳምንት ውስጥ እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ ሀውልቱ ቤተሰቦቻቸው የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ይመረቃል መባሉን የሰማን ሲሆን የመታሰቢያ ሀውልቶቹን የግንባታ ወጪ ሙሉ ለሙሉ በከተማ አስተዳደሩ መሸፈኑንም ሰምተናል። የጀነራል ሰዓረ መኮንን ሀውልት ቦሌ ሩዋንዳ አደባባይ አጠገብ እየተገነባ ሲሆን የአርቲስት ሀጫሉ ሀውልት ደግሞ ከመስቀል አደባባይ ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፊት ለፊት በአርቲስቱ በተሰየመው ፓርክ ውስጥ መቆሙ ይታወቃል። ጀነራል ሰዓረ መኮንን ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ደግሞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተገደሉ አስታውሶ የዘገበው ኢቢሲ ነው።