EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሳሰቢያ

የንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ የመሰሉ ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን የምትጠቀሙ  ደንበኞቼ እባካችሁ ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ ብሏል።

ባንኩ ለደንበኞች ባወጣው ማሳስቢያ የዲጂታል የክፍያ ስርዓት እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ አጭበርባሪዎች ቀደም ሲል የተከፈለን የክፍያ ደረሰኝ ወይም ሀሰተኛ የክፍያ ደረሰኝ ሞባይላቸው ላይ አሳይተው ክፍያ የፈፀሙ በማስመሰል ስርቆት እንደሚፈጽሙ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

በመሆኑም ተጠቃሚዎች ክፍያዎችን በዲጂታል አማራጮች ሲቀበሉ ከፋዩ ከሚሰጠው ማረጋገጫ በተጨማሪ ፣ ከባንኩ በሚላከው አጭር የፅሁፍ መልእክት ወይም ሂሳብዎን በመክፈት ክፍያው በትክክል ወደ ሂሳብዎ መግባቱን አረጋግጡ ሲል ባንኩ አስጠንቅዋል ::