EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 2.4 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት በሰጡት መግለጫ ባንኩ በ2025/26 በጀት ዓመት 707 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ቁጠባ መሰብሰቡንና አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ወደ 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር ማድረሱን ገልጸዋል።

ባንኩ በዘንድሮው በጀት ዓመት 80 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንና 648 ቢሊዮን አዲስ ብድር መስጠቱን ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ በቀጣዩ ዓመት 832 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ለማሰባሰብ እንዲሁም ገቢውን 360 ቢሊየን ብር ለማድረስ ማቀዱን በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews