የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክልል ደንበኞቹ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀሩት ክልሎች ያሉ ደንበኞቹ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ መረጃቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ የተቀመጠው ቀነገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ እንደቀሩት አስታወቀ።
ባንኩ ይሄን ያለው ደንበኞቹ በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ ማስተሳሰሪያ አማራጭ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ መረጃዎቻቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ ባሳሰበት መግለጫ ላይ ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በሀገሪቱ በተመረጡ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ መረጃቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ የተቀመጠው ቀነገደብ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ማብቃቱ ይታወሳል፡፡ መረጃው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
