EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ና የአስመራ በረራ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረረ እንደሚያቋርጥ ገለፀ።
አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው በረራውን ለማቋረጥ የተገደደው በአስመራ ባጋጠመው ከአቅም በላይ የሆነ የአሰራር ችግር መሆኑን ተናግሯል።
ቀድመው ትኬት ለቆረጡ ደንበኞቹ ሙሉ ገንዘባቸው እንደሚመልስ ገልጾ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌላ አየር መንገድም እንዲጠቀሙ የሚያደርግ አማራጭ አስቀምጧል።