የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ… ለታንዛኒያ
ኢትዮጵያ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለታንዛንያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሙከራ ሽያጭ እንደምትጀምር ተገለፀ፡፡
ወደታንዛንያ የሚደረገው የሙከራ ሽያጭ ሂደቱ በስኬት ከተጠናቀቀ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ሩብ ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች ተብሏል፡፡
በተያያዘም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለስልጣን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 20 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡