የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ስምምነት
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ግንባታ ዘርፍ መሰማራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።
በሁለቱ አገራት መካከል በመሪዎች ደረጃ የጋራ የልማት ትብብር በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ስምምነት መደረሱን ተከትሎ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከል በቤት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተደርሷል።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና የማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ኢማኑኤል አዲል በይፋ ፈርመዋል።
ይህ ውል ኮርፖሬሽኑ ያለውን ልምድና የቴክኒክ አቅም በመጠቀም በጁባ ከተማ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሕንፃዎችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲያከናውን ያደርገዋል።
መረጃው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
