EthiopiaNews

የኢትዮጵያ እና ጣሊያን ስምምነት

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የቀበና ገባር ወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ለመጀመር የሚያስችል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የቀበና ወንዝ ተፋሰስን ሥነ-ምህዳራዊ እና ማህበራዊ ገጽታ ለማሻሻልና ለማልማት ያለመ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አማካኝነት በ24 ወራት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ብክለት ያለባቸውን ሁለት የቀበና ወንዝ ገባሮችን መልሶ ለማልማት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እና የዝናብ ውሃ መውረጃዎችን ግንባታ ያካተተ ነው ተብሏል።

መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv