ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ የጭነት መጓጓዣ ጊዜ መውረዱ ተገለፀ።
ድርጅቱ ይሄን ያለው ከቱርክ ወደቦች የሚነሱ ገቢ ጭነቶችን በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻ ደረቅ ወደቦች የማጓጓዝ አዲስ አገልግሎት መጀመሩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።
ድርጅቱ በባለፉት 3 ወራት ብቻ 150 ሙሉ ኮንቴይነር ጭነቶች በሁለት ዙር ማጓጓዙን እና ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የጭነት መጓጓዣ ጊዜ ከ40 ቀናት ወደ 9 ቀናት ማውረዱን አሳውቋል።
ይህም ለኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎችን በፍጥነትና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማቅረብ አስፈላጊ መፍትሔ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።መረጃው ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
