EthiopiaNews

የእነ ዮሐንስ ዳንኤል የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ

የእነ ዮሐንስ ዳንኤል በርሄን የክስ መዝገብ ለመመልከት ችሎቱ ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል።
ፍርድ ቤቱ መስከረም 3 ባስቻለው ችሎት ለዛሬ መስከረም 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የክስ መዝገቡ በጠበቃቸው አማካኝነት የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ ቢቀርብም ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ሳይቀበለው መቅረቱ ተነግሯል።
የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ዮሐንስ ዳንኤልን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሶስት ክሶችን መመስረቱ የሚታወስ ነው፡፡