የእንግሊዝኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ
በትምህርት ሚኒስቴር፣ በዩናይትድ ኪንግደም የውጭ አገራት የጋራ ሀብት ልማት ቢሮና በብሪቲሽ ካውንስል መካከል በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሻሻል የሚያስችል የ5 ሚሊየን ፓውንድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በለንደን ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የአለም የትምህርት ፎረም 2026 ጎን ለጎን የተፈረመው ስምምነቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከርና ለማሻሻል የሚያስችል ነው ተብሏል።
እንዲሁም በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራን አቅምን ለማጎልበት እና የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ለማሳደግ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ስምምነቱ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ዓለም አቀፍ ትብብር የሚያጠናክር ነው የተባለ ሲሆን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን የቋንቋ ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል ነው የተባለው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
