የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኦላይን አማካኝነት እንደሚያከናውኑ ተገለፀ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኦላይን አማካኝነት እንደሚያከናውኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማህበራዊ ትስስር ገጽ እንዳስታወቀው ከሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኦላይን አማካኝነት ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ማለትም እስከ ሚያዝያ 26/2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን አስታውቋል።በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች –http://www.nebe.org.et/ovrs በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። በተጨማሪም ቦርድ ይህን የምዝገባ ሂደት በተመለከተ ለፓለቲካ ፓርቲዎች በማቅረብ ምክክር ተደርጎበታል ብሏል።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs