የካራማራ ድል በዓል በኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት ፓርክ እየተከበረ ነው

43ኛው የካራማራ ድል ክብረ በዓል በኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት ፓርክ እየተከበረ ይገኛል።በመታሰቢያ ዝግጅቱ ላይ በጦርነቱ የተሳተፉ የሠራዊቱ አባላት፣ አርበኞች፣ የኩባ ሪፐብሊክ አምባሳደር እና ድሉን ለማሰብ የተሰባሰቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ታድመዋል።የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆም ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር ያሳዩበት በመሆኑ ተመጣጣኝ ክብርና እውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጿል።