LatestNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትግራይ ስላለው ሁኔታ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት እና ግንኙነቷን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

በትግራይ ክልል የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ እና የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት ላይም ተወያይተዋል፡፡

አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡