InternationalNews

የኮቪድ ዳግም መከሰት

በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ የኮቪድ ዝርያ በመከሰቱ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ሳይንቲስቶች መግለፃቸው ታውቋል።

በሰኔ ወር ጀርመን ውስጥ እንደተገኘ የተነገረው ኤክስኢሲ የተሰባለው የኮቪድ ዝርያ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዴንማርክ እና በሌሎች በርካታ አገራት ውስጥ መከሰቱ ተገልጿል።

እስካሁን በ15 የአውሮፓ አገራት ተከስቷል የተባለው ቫይረሱ ቀድሞ ተከስቶ ከነበረው የኮቪድ ቫይረስ አንጻር የመተላለፍ ፍጥነቱ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑ እየተነገረ ነው።