EthiopiaNews

የኮንትሮባንድ እቃዎች

🔸የገቢዎች ሚኒስቴር ከ704 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።

🔸ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬድዋ፣ አዋሽ እና አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በተደረገ ክትትል 669.4 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እና 35.1 ሚሊዮን ብር የወጭ ኮንትሮባንድ በድምሩ 704.5 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

🔸በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

🔸የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 19 ተጠርጣሪዎች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

👉መረጃው ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews