EthiopiaNews

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት 3 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧን አስታወቀ።

ይህም ከአለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲወዳደር ከ16 በመቶ በላይ እድገት ማስመዝገቡን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ወቅት ከ370 በላይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን በመስጠት ከተቀመጠው ዕቅድ በላይ ተፈፃሚ መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም በኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026 ፎረም 7 ግዙፍ ስምምነቶችን በማፅደቅ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ካፒታል እንዲመዘገብ መደረጉ አገሪቱን እንደ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጕታል ተብሏል።

#EBS

#EBSTVNEWS

#EBSTVSPORT

#_7696_WN

https://t.me/ebstvnews

www.ebstv.tv