EthiopiaNews

ሚኒስቴሩ ይሄን ያስታወቀው በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ነው።

ሚኒስቴሩ በሳኡዲ አረቢያ ምህረት የተደረገላቸውን ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው በተከታታይ በረራዎች እየተመለሱ እንደሚገኙ ገልጿል።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ሰብዓዊ ምሕረት እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ፣ የቆንስላ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግና ተገቢው መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ከሚመለከታቸው የሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር ያለውን ውይይት አጠናክሮ መቀጠሉንም ሚኒስቴሩ አሳውቋል። መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።