የዝሆን አድን ጥሪ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዝሆንን ከመጥፋት እንታደግ ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡በትላንትናው እለት በአለም አቀፍ ደረጃ የተከበረውን የዝሆን ቀን አስመልክቶ ውይይት ያካሄደው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ያለው የዝሆኖች ቁጥር እጅጉን እየተመናመነ መምጣቱን ጠቅሶ ሁሉም ዜጋ ከመጥፋት እንዲታደገው ጥሪ አቅርቧል፡፡
እ.አ.አ ከ1980 ወዲህ ብዛታቸው እየተመናመነ መጥቶ በአሁኑ ሰአት ከ2ሺ የማይበልጡ ዝሆኖች በአገሪቱ እንደሚገኙ ለኢቢኤስ አዲስ ነገር የነገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ ለዝሆኖቹ መመናመን ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ለጥርሳቸው ሲባል መገደላቸው በዋናነት ይጠቀሳል ብለዋል፡፡
የሰው ቁጥር መጨመር፣የእርሻ ሰፈራና የሰውና ዝሆኖች ግጭትም ሌላው ምክንያት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ስለሆነም ባሉበት ተረጋግተው እንዲቆዩ ግድያን ዜሮ ማድረግ፣የሰዎች የመስፋፋት ሁኔታ በማስቆምና ስላሉበት ደረጃ ጥናትና ምርምር በማድረግ ከመጥፋት ልንታደጋቸው ይገባል የተባለ ሲሆን በቀጣይ በርካታ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፉ ጥናቶች እንደሚከናወኑና መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሆኑ ጠተይቋል፡፡

በነገራችን ላይ የኬንያ አየር መንገድና ዩ ኤስ ኤይድ ዝርያቸው በመመናመን ላይ የሚገኙ የዱር እንስሣት ህገወጥ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመዋል። በመድረኩ ላይ የኬኒያ አየር መንገድ ለባለድርሻ አካላት የሃገራትን ብሄራዊ ቅርሶች አጠባበቅን በተመለከት መረጃ የሚሰጥ ቪዲዮም አቅርቧል። ይህም እንቅስቃሴ የኬኒያ አየር መንገድ የአፍሪካን የዱር እንስሳ ደህንነት በማስጠበቅ የአህጉሪቱ ዘላቂ ልማት ላይ አሻራውን የማኖር እንቅስቃሴ አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us

ኢቢኤስ

EBS