የዝቅተኛ ደሞዝ እርከን ጥናት ተጠነቀቀ
መነጋገሪያ እየሆነ የመጣው እና በብዙ ሰራተኞችና የሰራተኛ ማህበራት ዘንድ የቅሬታ ምንጭ እንደሆነ የሚነገርለት ዝቅተኛ ደሞዝን የመወሰን ጉዳይ ጥናቱ መጠናቀቁ ተነግሯል።
በአገሪቱ የዝቅተኛ ደሞዝ እርከን ውሳኔን ተግባራዊ ለማድረግ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቆ ምክክር እየተደረገበት እንደሚገኝ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይህንን ያለው ከክልል የዘርፉ አመራሮች ጋር ሰሞኑን በመከረበት ወቅት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።