EthiopiaNews

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በተለያዩ የአለም ሀገራት እየተሰራጨ የሚገኘውን ሞንኪ ፖክስ ወይም በተለምዶ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ጎረቤት ሀገር ኬንያ መገኘቱን ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊና ኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ የመግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ እንዲሁም በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የቅኝትና የቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የድከም ስሜት፣ የቆዳ ሽፍታና ቁስለት እንዲሁም የጡንቻና የጀርባ ህመም በበሽታው የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ሲሆኑ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በሚኖር ንክኪ ወይም ከበሽታው ከተያዘ እንስሳ በሽታው ሊተላለፍ እንደሚችል ተገልጿል።