News

የዩኤስ ኤይድ እርዳታ መቀጠል

የአሜሪካው የልማት ተራድኦ ድርጅት ላለፉት አምስት ወራት በኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን የሰብአዊ ድጋፍ በሚቀጥለው ወር ሊያስጀምር መሆኑ ተነግሯል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ በሚያካሂደው የድጋፍ ስራ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከረድኤት ድርጅቶች ጋር ከመግባባት መድረሱን ተከትሎ ነው በሚቀጥለው ወር የሰብዓዊ ድጋፉን እንደሚያስጀምር ያስታወቀው።
የተራድኦ ድርጅቱ አክሎም ድጋፉ ለቀጣይ አንድ አመት የሚቀጥል መሆኑንና ይህ መቀጠሉም በኢትዮጵያ የሚተገብራቸውን የአሰራር ማሻሻያዎች ለመገምገም እድል የሚፈጥር ነው ብሏል::

ዩኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ ለሚተገብረው የእርዳታ አሰጣጥ ማሻሻያ ስራዎች የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ መስጠቱንም ነው ከሮይተርስ ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው።