EthiopiaNews

የንፋስ ኃይል

የአዋጭነት ጥናታቸው የተጠናቀቁ 18 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስሪያ ቤት አስታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ከተገነቡ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 404 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መቻሉን ያሳወቀው መስሪያ ቤቱ አዲሶቹ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ተጨማሪ ሁለት ሺ 700 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖራቸዋል ብሏል፡፡
ኘሮጀክቶቹ የሚገነቡበትን በጀት በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ያስታወቀው መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የንፋስ ኃይል ያለባቸው ጎዴ፣ ቀብሪበያህ፣ እንዲሁም የተለያዩ የትግራይ፣ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ከካባቢዎች ላይ እንደሚካሄድ ጠቁሟል።

መረጃው የኢኤኃኮ ነው