EthiopiaNews የጀርመን ድጋፍ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች September 5, 2024 Frehiwot ጀርመን ለኢትዮጵያ የ4.4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የጀርመን መንግስት የሚያደርገው ድጋፍ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች በነበረው አውዳሚ ጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።