EthiopiaNews

የገንዘብ ሚኒስቴር

የገንዘብ ሚኒስቴር የተቋሙን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስራ ግብር ቅናሽ ተደርጓል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀሰተኛ ነው ሲል ያሳወቀው ደብዳቤው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴን የሀሰት ስምና ፊርማ በመጠቀም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የስራ ግብር ቅናሽና የደሞዝ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የሚያዝ ነው፡፡

በመሆኑም ይህ በሃሰት እየተሰራጨ የሚገኝ መረጃ የተቋሙ እውቅና የሌለው መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስለተቋሙ ስራዎች ትክክለኛ መረጃዎችን የገንዘብ ሚኒስቴር የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን  በመከተል ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/