የጋራ ግብረሃይሉ መግለጫ
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫው ወቅትና ከምርጫ በኋላ ያሉ ሥራዎችን እንደ ሀገር ዕቅድ አውጥቶ በቅንጅት በመምራቱ ምርጫው በሰላም ሊጠናቀቅ መቻሉ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የግብረ-ኃይሉን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፀጥታና ደኅንነት አፈፃፀም ሪፖርት የገመገመ ሲሆን የጋራ ግብረ-ኃይሉ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደናቀፍ በሀገር ውስጥና በውጭ ጠላቶች የተቀናጀውን ሴራ ማክሽፉ በዚሁ ወቅት ተነግሯል።
በቀጣይም በሽብርተኞችና በፅንፈኞች ላይ የተጀመረው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን የምርጫው ውጤት ታውቆ አዲስ የመንግሥት ምስረታ እስከሚከናወንበት እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ያሉ ሕዝባዊና መንግስታዊ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ ሥራው ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
