EthiopiaNews

የግዥ ስምምነት

የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከአሜሪካው የቦይንግ ኩባንያ ስድስት 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ግዢ ለመፈጸም ስምምነት ተፈራረመ።

ቦይንግ ኩባንያ ባወጣው መግለጫ አየር መንገዱ የግዥ ስምምነት የተፈራረመባቸው ስድስት 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች የካርጎ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማስፋፋት የሚውሉ ናቸው ብሏል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ 6 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ከቦይንግ በመግዛቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው አየር መንገዱ በአስተማማኝ እድገት ላይ ነው ብለዋል።

የቦይንግ የአፍሪካ ቀጠና የሽያጭ ምክትል ፕሬዝዳንት አንበሴ ይትባረክ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የገዛቸው አዳዲስ አውሮፕላኖች ተጨማሪ መዳረሻዎች እንዲጀምር ይረዳዋል ብለዋል።

መረጃው ከቦይንግ ኩባንያ የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv