Ethiopia

የጤና ዘመቻ

የጤና ሚኒስቴር በ8 ክልሎች እና በ154 ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረግ ትምህርት ቤቶችን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ መጀመሩን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው አገር አቀፍ የጤና ዘመቻው ትናንት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

በዘመቻው የብልሃርዚያና የአንጀት ትላትል መድሀኒት እደላ፣ የኤች ፒ ቪ ክትባት፣ የቲቢ መለየት ፣ የአይን ምርመራ፣ የደም ግፊት እና የስርዓተ ምግብ ምርመራ ያካተተ አገልግሎቶችን ለተማሪዎች ይሰጣሉ ተብሏል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እንደገለፁት ት/ቤት ላይ እንዲህ አይነት ስራዎች መስራት ለጤና አገልግሎት ተደራሽነት የሚረዳ ስለሆነ ጤናን ከተለያዩ ዘርፎች ጋር በማቀናጀት በርከት ያሉ የጤና አገልግሎት ስራዎችን ት/ቤትን ማዕከል አድርጎ ይሰራል ብለዋል።

መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv