የጦር መሳሪያ እና ወታደሮችን እያጓጓዘ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሰው የሃሰት ወሬ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የጦር መሳሪያ እና ወታደሮችን ወደ ትግራይ ክልል እያጓጓዘ ነው በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሰው የሃሰት ወሬ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ አየር መንገዱ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው ካሳለፍነው ህዳር ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በረራዎች ተቋርጠው የነበር ቢሆንም በመሃል ግን በተከፈተበትም ወቅት አስፈላጊ የንግድ በረራዎች ብቻ እንደተካሄዱበት አስታውቋል።ይህን ተከትሎም በየትኛውም ወቅት ላይ ወደ ግጭት ቀጠናዎች የበረራ አገልግሎት ሰጥተን እነደማናውቅ እና አንዳንድ ግለሰቦች አየር መንገዱ የገነባውን መልካም ስም ለማጉደፍ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የቆዩ ፎቶግራፎችን እና የተሳሳቱ ምስሎችን በፎቶሾፕ በማቀነባበር በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።መለዮ ለባሽ ወታደሮች በህዝብ ትራንስፖርት መገልገላቸው የተለመደ ዓለም አቀፍ አሰራር ቢሆንም አየር መንገዱ ግን ጦርነት ወዳለባቸው አካባቢዎች አጓጉዟል ማለት አለመሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለንም ሲል አስነብቧል።። ስለዚህም አጠቃላይ ማህበረሰቡን ጨምሮ ደንበኞቻችን፣ የስራ አጋሮቻችን እና ባለድርሻ አካላትን አየር መንገዱ የቀረበበት ከእውነት የራቁ የስም የማጥፋት ዘመቻዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንወዳለሁ ብሏል።