አዲስ ነገር – የጭነት አገልግሎት ክብረወሰን

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ የጭነት አገልግሎቱ በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያው ሩብ አመት 50 ሚሊዮን ያህል የኮቪድ 19 መመርመሪያ መሳሪያዎችን ከደቡብ ኮሪያ ወደ ዩናይትድ ስቴስ አሜሪካና ካናዳ በማጓጓዝ አዲስ ክብረወሰን መስበሩ ተገለጸ፡፡
አየር መንገዱ በ61 በረራዎች 3 ሺህ 200 የካርጎ ጭነቶች ከደቡብ ኮሪያ ወደ አሜሪካና ካናዳ ያጓጓዘ ሲሆን መመርመሪያ መሳሪያዎቹን በታቀደለት ጊዜ እንዳከናወነም በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎት የ2022 የአለማችን ምርጡ የካርጎ ጭነት አገለግሎት ሰጭ ለመባል ለውድድር መብቃቱንና ሽልማቱን ለማግኘትም ተገለጋዮቹ ድምጽ እንዲሰጡት ከቀናት በፊት ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New