Sports

EBS SPORT – የምሥራቅ አፍሪካ ከ20 አመትና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡

ውድድሩ በታንዛኒያ ዳሬሰላም  ግንቦት 6 እና 7  ሊደረግ ቀነ ቀጠሮ ቢያዝለትም የውድድሩ አዘጋጆቹ ለውድድሩ ማከናወኛ  የሚሆን በጀት ከአለም አትሌቲክስ በወቅቱ ስላልተላከላቸቸው ውድድሩን ማራዘማቸውን በደብዳቤ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቀዋል፡፡

በውድድሩ ተሳታፊ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ዝግጅቷን አጠናቃ በትላንትናው እለት ለልኡክ ቡድኑ  ሽኝት ለማድረግ አቅዳ የነበረ ቢሆንም መርሃ ግብሩ መራዘሙን ተከትሎ የሽኝት ፕሮግራሙ ሳይካሄድ መቅረቱ ተዘግቧል   የምሥራቅ አፍሪካ ከ20 አመትና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናው በ 13 ቀናት ተገፍቶ ግንቦት 19 እና 20 እንደሚካሄድም ተነግሯል ፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከ 7:00 ሰዓት እስከ 7:30 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መረጃዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New