የጸሎት መርሃ ግብር
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የጸሎት መርሐ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።
የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህ የጸሎት መርሃ ግብር 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ እንዲሁም ሰላም ይበልጥ ይፀና ዘንድ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
መርሃ ግብሩ በአደባባይ ደረጃ የሚከናወን በመሆኑ በመጪው ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የየእምነቱ ተቋማት መሪዎች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት በአራዳ ፓርክ ይከናወናል ተብሏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም ተጠቁሟል።
ጉባኤው ጸሎቱ ፍጹም ሰላማዊና ሃገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከናወን ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ጠቁሟል።
በመሆኑም በመላው ኢትዮጵያ ለሚካሄደው ለዚሁ የጸሎት መርሃ ግብር ሁሉም የሃይማኖት ተቋማትና ምዕመናን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጉባኤው ጥሪውን አስተላልፏል።
እንዲሁም ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች ለሃገራቸው ሰላም ሲሉ በዚህ ታሪካዊ መርሃ ግብር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጉባኤው ጥሪውን አቅርቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
