InternationalLatestNews

የፈረንሳይ ወታደሮች ከማሊ ለቀው ወጥተዋል፡፡

የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ ከታሪካዊዋ የቲምቡክቱ ከተማ ለቀው ወጥተዋል፡፡ ፈረንሳይ በማሊ ያላትን ወታደሮች ትላንት ማስወጣት የጀመረች ሲሆን ከቲምቡክቱ መውጣቷም ለውሳኔዋ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ሆኗል፡፡የፈረንሳይ ወታደሮች ከ9 አመታት በፊት ወደ ማሊ ሲዘምቱ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ፍራንሲስ ሆላንዴ ወታደራዊ ስምሪቱን ይፋ ያደረጉት ከቲምቡክቱ ከተማ ነበር በመሆኑም የፈረንሳይን ከከተማዋ መውጣት ምሳሌያዊ ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡ቢቢሲ እዳለው ታሪካዊቷን የቲምቡክቱ ከተማ ሲጠብቁ የነበሩት የፈረንሳይ ወታደሮች አዛዥ የከተማዋ ቁልፍ የተባለውን የእንጨት ጌጥ ለማሊ ወታደሮች አዛዥ አስረክበዋል፡፡በማሊ ከአንድ አመት በፊት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተሞከረ በኋላ በሀገሪቱ መንግስትና በፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት በእጅጉ መሻከሩ ይገለጻል፡፡በዚሁም የተነሳ ፈረንሳይ በሰሜናዊ ማሊ ያሉ የወታደሮችዋን ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰች ነው፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

30302 CommentsLikeCommentShare