EthiopiaNews

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለዘላቂ ሰላም ሲባል የተከፈለ ትልቅ ዋጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ሲሆን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ግጭትን ለማቆም የተከፈለ ዋጋ ነው ብለዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስት መቋቋሙን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ60 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን በተሀድሶና መልሶ ለማቋቋም የስልጠና ማእከላት እንዲቋቋሙ መደረጉን ገልጸዋል።

በክልሉ አሁንም የሰላም ማወክ ጥረቶች መኖራቸውን ጠቅሰው እታገልልሃለሁ በሚሉት ኃይሎች የተነሳ የትግራይ ህዝብ በሰላም ወጥቶ መግባት እንዳልቻለም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም መንግስት የሰላም መደፍረስ ምንጩን በሚገባ የሚያውቅ መሆኑንና ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አስተማማኝ አቅም እንዳለውም ነው ያብራሩት፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv