የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ቀብር
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ሰምተናል።
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባደረባቸው ሕመም በኬንያ ናይሮቢ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ትናንት መስከረም 7 ቀን 2017 ዓም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል። አስክሬናቸውም ትናንት ምሽቱን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡