የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 እንደሚሰጥ ተገለፀ

ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29/2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ገልጸዋል።

ከየካቲት 21-27/2013 ዓ.ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
ምንጭ:- ትምህርት ሚኒስቴር