LatestNews

አበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ተመረቀ

በኢትዮጵያ ትልቁ እና ዘመናዊ የተባለው የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል ተመረቀ፡፡

ሆስፒታሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መርቀውታል፡፡

ሆስፒታሉ በ700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ከ400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

በ22 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈው ሆስፒታል በተመሳሳይ ሰአት ሰባት እናቶችን በቀዶ ጥገና ማዋለድ የሚያስችል አቅም አለውም ነው የተባለው።

በተጨማሪም 100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በምርቃት ስነ ስርአቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የሃይማኖት አባቶች የክብር ዶክተር አበበች ጎበናን ጨምሮ የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡