EthiopiaNews

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና

🔸የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ታዛቢዎች በሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት እንዲሁም በምርጫ ወቅት ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ጥቃቶች አስመልክቶ ሥልጠና መስጠቱን አስታወቀ።

🔸ቦርዱ ይህንን ያስታወቀው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መታዘብ ላይ ለተሠማሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት እንዲሁም በምርጫ ወቅት ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ ሥልጠና በሰጠበት ወቅት ነው።

🔸ለ43 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የተሰጠው ሥልጠና በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በሥርዓተ-ፆታ ዕኩልነትና ማኅበራዊ አካታችነት ነው ተብሏል።

🔸በተጨማሪም በቦርዱ በሴቶች ላይ የሚደርሱ የሥነ-ልቦና፣ የአካልና የዲጂታል ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀ ስላለው የጋራ የአሠራር መመሪያና የባለድርሻ አካላት ልየታን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

🔸ቦርዱ ከተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት ጋር በመተባበር ያካሄደው ይሄ ሥልጠና የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሣትፎ ከፍ ለማድረግና የሚያጋጥሟቸውንም ተግዳሮቶች መፍትሔ ለመስጠት ከሚሠራቸው በርካታ ሥራዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews