የ2020/2021 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ዛሬ ዓርብ ሃምሌ 16 በይፋ ይጀመራል፡፡

የ2020/2021 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ነገ በይፋ የሚጀመር ይሆናል። በዚህም ሃገራችን ኢትዮጵያ በ 4 ዘርፎች ተሳታፊ ትሆናለች።እነዚህም ዘርፎች ቴኳንዶ ፤ ብስክሌት፤ የውሃ ዋና እና አትሌቲክስ ናቸው።
በውድድሩ ላይም ስመጥር የሚባሉና ከዚህ ቀደም ሃገራችንን ያስጠሩ አትሌቶች ይገኙበታል። በተጨማሪነትም ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ላይ በ13 ዘርፎች ላይ ተሳታፊ ትሆናለች። በ800 ሜትር በወንዶች እና በሴቶች ፣ በ1500 ሜትር በወንዶች እና በሴቶች ፣ በ3000 ሜትር መሰናክል በወንዶች እና በሴቶች ፣ በ10000 በወንዶች እና በሴቶች ፣ ማራቶን በወንዶች እና በሴቶች እንዲሁም በእርምጃ ሴቶች ተሳታፊ ይሆናሉ።በ10000 ሜትር በወንዶች ሩጫ ላይም የሚሳተፉ ተወዳዳሪ አትሌቶች የፊታችን ቅዳሜ ለወድድሩ ጉዞአቸውን ያደርጋሉ። እንዲሁም በ13ቱ ዘርፍ ላይ ማን ማን ተሳታፊ ይሆናል ሚለውን ከሰአታት በኋላ የምናሳውቅ ይሆናል ተከታተሉን።
መልካም እድል ለሁላችን!!!