ድጋፍ በአማራ ክልል
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአማራ ክልል ከ100,000 በላይ ለሆኑ ህሙማን ነፃ የህክምና ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ኮሚቴው ባለፉት ሳምንታት በምስራቅ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ጎጃም ላሉ አራት የጤና ማዕከላት አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ኮሚቴው በአማራ ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላሉ ሰዎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን ማግኘት የዕለት ተዕለት ትግል ሆኖ መቆየቱን ገልጾ ማህበረሰቦች የሚያስፈልጋቸውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለመርዳት እየሰራሁ ነው ብሏል።መረጃው ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
