InternationalNews

ግብፅ መሬት ቆርጣ መሸጥ ስለመጀመሯ እንገራቹ

ግብፅ የገጠማት የኢኮኖሚ ምስቅልቅል የባህር ዳርቻዎቿን ለባህረ ሰላጤው ሃገራት በጨረታ ቆርጣ እስከመሸጥ እንዳደረሳት ምንጮች አስታውቀዋል።

የግብፅን መሬት ዋነኛ ገዢ ሆና የቀረበችው ሳዑዲ አረብያ በቀይ ባህር ዳርቻ ቁልፍ አቀማመጥ ያለውን የራስ ጀሚላ የቱሪስት መዳረሻ ለመግዛት ለካይሮ መንግስት ጥያቄዋን አቅርባለች።
8 መቶ 60 ሺህ ስኴር ሜትር የቆዳ ስፋት ያለው የራስ ጀሚላ የባህር ዳርቻ ሳዑዲ አረብያ አልቆላት ከገዛችው በአካባቢው ይዞታዋን እንድታጠናክር የሚረዳት ሲሆን ቦታው ወሳኝ የሆነ የጂኦፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጠቀሜታ እንደሚያስገኝላት ታምኖበታል።

ሳዑዲ በግብፅ ብሔራዊ ባንክ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ሲኖራት ይህንን ተጠቅሜ የባህር ዳርቻውን ልግዛሽ ስትል ግብፅ በበኩሏ ይህን በእጇ የገባውንና የሳዑዲ አረብያ ረብጣ ዶላር ለማስቀረት መጎምዠቷ ጥያቄውን ልትቀበል እንደምትችል ግምት አሰጥቷል።

ከዚሁ የግብፅ መሬት ሽያጭ ሳንወጣ፤ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት የካቲት ወር ግብፅ ለዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በሜድትራኒያን የባህር ዳርቻ የሚገኘውን የራስ ሄል ሂክማ ቁልፍ መሬቷን እንድታለማ በሚል የ35 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ፈርማለች። ከዚህ ከፍተኛ ገንዘብ ውስጥ 11 ቢሊየን ዶላሩ አሁንም በግብፅ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ የተቀመጠ መሆኑ ታውቋል።

ግብፅ ሉዓላዊ ግዛቶቿን ለችርቻሮ እንስከማቅረብ ያደረሳት ያለባት ከፍተኛ የውጪ እዳ ጫና መሆኑን ነግረናቹ አበቃን።
ለጥንቅሩ ባልደረባችንን ግርማዬ ከበደን እናመሰግናለን።